የፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ. 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ

የፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ. 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ህዳር 24 ቀን 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል ተካሂዷል፡፡

በጉባኤው ላይ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ፈንቴ ጥሪውን አክብረው በጉባኤው ላይ የተገኙትን ባለአክሲዮኖች በማመስገን ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን በንግግራቸውም፡-

  • የፀሐይ ኢነዱስትሪ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ ለ2014 በጀት ዓመት በዕቅድ የተያዙ ልዩ ልዩ ተግባራት በአግባቡ እንዲከናወኑ ለአክሲዮን ማህበሩ ማኔጅመንት ተገቢውን አመራርነና አቅጣጫ የመስጠት፣ የመከታተልና ተገቢውን ድጋፍ የማድረግ ተግባር ማከናወኑን
  • በበጀት ዓመቱ ካለፉት ዓመታት በጣም በከፋ ደረጃ በሀገራችን በተፈጠረው የባንክ የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ዕጥረት የተነሣ በቂ ጥሬ ዕቃ ለመግዛት ባለመቻሉ የምርትና የሽያጭ አፈፃፀም ከአቀድነው አንፃር ያነሰ ቢሆንም የችግሩን መጠን በተወሰነ ደረጃ ለመቀነስ ይቻል ዘንድ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትና ማኔጅመንቱ ከበርካታ ከግል ባንኮች ጋር በተፈጠረው ጠንካራ የስራ ግንኙነትና ክትትል የተነሣ በተገኘው መጠነኛ የውጭ ምንዛሬ በተገዛው ጥሬ ዕቃ በገበያ ተፈላጊ የሆኑ ምርቶች ላይ በማተኮር ተመርተው በተቻለ መጠን ወቅታዊ በሆነ የገበያ ዋጋ እንዲሸጡ በመደረጉ እና ከዚሁ ጎን ለጎን የወጪ ቅነሳና ቁጥጥር ትኩረት ተሰጥቶ በመከናወኑ የአክሲዮን ማኅበራችን የ2014 በጀተት ዓመት የትርፍ አፈፀፃፀመም ከባለፉት ዓመታት ሁሉ መብለጡን፣
  • በበጀት ዓመቱ በተለያዩ ምክንቶች የታሰበውን ያህል ምርትና ሽያጭ ለማከናወን ባይቻልም የድርጅቱን ትርፋማነት ለማስቀጠል በመቻሉ የድርጅቱን ማኔጅመንትና ሠራተኞች፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን፣ ባለአክሲዮኖችን እንዲሁም አጋር ድርጅቶችን ድጋፍና እገዛ በማድረጋቸው ሁሉንም አመስግነዋል፡፡
  • በዕለቱ፡

    • የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት እና ታፈሰ፣ ሺሰማ እና አያሌው የተፈቀደለት ኦዲተር አማካይነት የውጭ ኦዲት ሪፖርት ለተሰብሳቢዎች ቀርቦ ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ ፀድቀዋል፣