የፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ. 12ኛ መደበኛና 7ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ተካሄደ

የፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ. 12ኛ መደበኛና 7ኛ አሰስቸኳይ ጉባኤ ታህሳስ 20 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል ተካሂዷል፡፡

በጉባኤው ላይ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ፈንቴ ጥሪውን አክብረው በጉባኤው ላይ የተገኙትን ባለአክሲዮኖች በማመስገን ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን በንግግራቸውም፡-

  • የፀሐይ ኢነዱስትሪ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ ለ2015 በጀት ዓመት በዕቅድ የተያዙ ልዩ ልዩ ተግባራት በአግባቡ እንዲከናወኑ ለአክሲዮን ማህበሩ ማኔጅመንት ተገቢውን አመራርና አቅጣጫ የመስጠት፣ የመከታተልና ተገቢውን ድጋፍ የማድረግ ተግባር በዚህ የበጀት ዓመትም ማከናወኑን
  • በበጀት ዓመቱ ካለፉት ዓመታት በጣም በከፋ ደረጃ በሀገራችን በተፈጠረው የባንክ የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት ዕጥረት የተነሣ በቂ ጥሬ ዕቃ ለመግዛት ባለመቻሉ የምርትና የሽያጭ አፈፃፀም ከአቀድነው አንፃር ያነሰ መሆኑን ገልፀው የችግሩ መጠን የከፋ እንዳይሆን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትና ማኔጅመንቱ በወሰዱት አማራጭ የመፍትሔ ዕርምጃዎች የተነሳ በተገኘው ውስን የውጭ ምንዛሬ አማካኝነት በተገዛው ጥሬ ዕቃ በገበያ ተፈላጊ የሆኑ ምርቶች ላይ በማተኮር ተመርተው በተቻለ መጠን ወቅታዊ በሆነ የገበያ ዋጋ እንዲሸጡ በመደረጉ እንዲሁም ከዚሁ ጎን ለጎን የወጪ ቅነሳና ቁጥጥር ስራ በመከናወኑ ማኅበራችን አትራፊ ሆኖ እንዲቀጥል መደረጉን፣
  • በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ በተለያዩ ምክንያቶች የታቀደውን ያህል መጠነን አፈፃፀም ባይመዘገብም የድርጅቱን ትርፋማነት ለማስቀጠል በመቻሉ የድርጅቱን የሥራ ሀላፊዎችና ሠራተኞች፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን፣ የተከበሩ ባለአክሲዮኖቻችን እንዲሁም አጋር ድርጅቶችን ድጋፍና እገዛ በማድረጋቸው ሁሉንም ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል፡፡
  • በዕለቱ፡

    • የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት፣ 7ኛ አስቸካይ ጉባዔ ሰነድ እንዲሁም በታፈሰ፣ ሺሰማ እና አያሌው የተፈቀደለት ኦዲተር አማካይነት የውጭ ኦዲት ሪፖርት ለተሰብሳቢዎች ቀርበው ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ ፀድቀዋል፣