አዲስ የተሳቢ፣ የደረቅ ጭነት አካላት እንዲሁም የፈሳሽ ጭነት ማመላለሻ (ቦቴ) ምርት በገበያ ላይ ዋለ

ድርጅቱ ቀደም ብሎ ያመርታቸው ከነበሩትና በጥራት ደረጃቸው ታዋቂ ከሆኑት ምርቶቹ በተጨማሪ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ተሳቢና የጭነት አካላት እንዲሁም የፈሳሽ ጭነት ማመላለሻ (ቦቴ) ዲዛይን በማድረግ አምርቶ መሸጥ መጀመሩን ሲገልፅ በደስታ ነው፡፡

ተሳቢዎቻችንና የጭነት አካላት እንዲሁም የፈሳሽ ጭነት ማመላለሻ (ቦቴ) ምርቶቻችን ዓለም አቀፍ ደረጃን አሟልተው ዲዛይን የተደረጉና የተፈበረኩ ስለሆነ ከማንኛውም ስጋት ነፃ ናቸው፡፡

የቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካን የተሳቢና የጭነት አካላት እንዲሁም የፈሳሽ ጭነት ማመላለሻ (ቦቴ) ምርቶች ልዩ የሚያደርጋቸው፡-

  • አከስልና ሰስፔንሽናቸው በጥንካሬውና አስተማማኝነቱ የታወቀውና ለከባድ ሥራ የሚያገለግለው BPW TRIDEM ሲሆኑ የተመረቱትም 3*12 ቶን የመሸከም አቅም ካለው አራት ማዕዘን ቱቦ መሆኑና አካሉም የጀርመን ስሪት መሆኑ፣
  • ፍሬኑ (Brake System) የተሠራው ከዝነኛው WABCO ብራንድ መሆኑ፣
  • ምርቶቹ በአንድ እጅ ዝገት መከላከያና በሁለት እጅ ኒትሮ የተቀቡ መሆኑ፣
  • የመጨረሻው ቀለም በደንበኞች ምርጫ መወሰኑ፣
  • ምርቶቹን በአጭር ቀጠሮ ለደንበኞች ማቅረብ መቻሉ እና
  • ከሽያጭ በኋላ ያለው አስተማማኝ አገልግሎቱ ናቸው፡፡